La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 22:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ስለ ክርስቶስ ምን ትላላችሁ? የማንስ ልጅ ነው?” እነርሱም “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው?” እነርሱም፣ “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ስለ መሲሕ ምን ትላላችሁ? የማንስ ልጅ ይመስላችኋል?” እነርሱም “የዳዊት ልጅ ነው” ሲሉ መለሱለት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 22:42
24 Referencias Cruzadas  

“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤


የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ መጽሐፍ።


በጀልባዋ የነበሩትም “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።


ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


እርሱም እንዲህ አላቸው፥ ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ እንዴት ጌታ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦


ኢየሱስ ከዚያ አልፎ ሲሄድ ሁለት ዓይነ ስውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።


ናትናኤልም መልሶ “መምህር ሆይ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” አለው።


ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት።


በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።