ማቴዎስ 21:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይዘውም ከወይኑ አትክልት ሥፍራ አውጥተው ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዘውም ከወይኑ ዕርሻ ውጭ አውጥተው ገደሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁንም ይዘው ከወይን አትክልቱ ቦታ ውጪ ወሰዱና ገደሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት። |
እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም።”