ማቴዎስ 19:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትህንና እናትህን አክብር፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤ የሚሉት ትእዛዞች ናቸው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባትህንና እናትህንአክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። |
እርሱም መልሶ፦ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ፤” አለው።
“አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ አትመኝ፤” የሚለው እና ሌላም ትእዛዝ ቢኖር፤ በዚህ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።
“ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር።