“ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን።
ማቴዎስ 16:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠበቁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ልብ አድርጉ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው። |
“ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን።
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ጥምቀት ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አመለከታችሁ?
በዚያን ጊዜ፥ በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ከብዛታቸው የተነሣ እየተረጋገጡ ሳለ፥ በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ እርሱም ግብዝነት ነው።