La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 14:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም “ና” አለው። ጴጥሮስም ከጀልባዋ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ በውሃው ላይ ተራመደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም፣ “ና” አለው። ጴጥሮስም፣ ከጀልባው ወርዶ በውሃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም “ና!” አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ በባሕሩ ላይ ተራመደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውሃው ላይ ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 14:29
10 Referencias Cruzadas  

ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንህ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” ሲል መለሰለት።


ነገር ግን የነፋሱን ብርታት አይቶ ፈራ፤ መስጠም በጀመረም ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ” ብሎ ጮኸ።


እርሱም የእምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ “ከዚህ ወደዚያ ሂድ” ብትሉት ይሄዳል፤ የሚያቅታችሁ ምንም ነገርም የለም።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ፥ በበለሲቱ ዛፍ እንደተደረገው ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤


ኢየሱስም፥ “የሚቻልህ ከሆነ አልህ? ለሚያምን ሰው ሁሉም ነገር ይቻላል” አለው።


ጌታም አለ፦ “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል፤’ ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።


በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፤ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።


መቶ ዓመት ሆኖት ሳለ ምውት የሆነውን የራሱን አካልና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆን አስቦ በእምነት አልደከመም፤


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።