La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 7:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፥ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳን አድርጓል” አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፣ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቈሮዎች እንዲሰሙ፣ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳ አድርጓል” አሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሰሙትም ሁሉ እጅግ በጣም በመደነቅ፦ “ሁሉን ነገር በመልካም አደረገ! ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ ያደርጋል!” አሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያለ መጠንም ተገረሙና “ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል፤” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያለ መጠንም ተገረሙና፦ ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ።

Ver Capítulo



ማርቆስ 7:37
16 Referencias Cruzadas  

እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።


ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፥ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።


በዚያም ቀን ደንቆሮዎች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፥ የዕውሮችም ዐይኖች ጭጋግና ጨለማው ተገፎላቸው ያያሉ።


እየወጡ እያለ እነሆ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።


ሕዝቡ በሙሉ በመደነቅ፥ “ይህ ምንድነው? በሥልጣን ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው?” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ።


እርሱም ተነሥቶ ሁሉም እያዩት ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ ሄደ፤ ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም፤” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።


እጅግም ፈሩና “እንዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።


ልጅቱም ወዲያውኑ ተነሥታ ቆመች፤ መራመድ ጀመረች፤ ዕድሜዋም ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ ሰዎቹም እጅግ በመደነቅ ተደመሙ።


እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ፀጥ አለ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤


ኢየሱስ ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤ ሆኖም እርሱ እንዳይናገሩ ባዘዛቸውም መጠን፥ ነገሩን አስፍተው አወሩት።


በዚያን ጊዜ፥ እንደገና ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ። የሚበሉት ምንም ምግብ ስላልነበራቸው ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲህ አላቸው፤


እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው።


ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ “አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል፤” አሉ።