La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 5:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤት በደረሱ ጊዜ፥ ሲታወኩ፥ ሰዎቹም ሲያለቅሱና አምርረውም ሲጮኹ ተመለከተ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤት እንደ ደረሱ፣ ኢየሱስ ግርግሩንና ሰዎቹም ዋይ ዋይ እያሉ አምርረው ሲያለቅሱ ተመለከተ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ምኲራብ አለቃው ቤት በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ሰዎቹ ሲንጫጩና ሲያለቅሱ፥ ሲጮኹም ተመለከተ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤

Ver Capítulo



ማርቆስ 5:38
8 Referencias Cruzadas  

‘ዋሽንት ነፋንላችሁ አልጨፈራችሁም፥ ሙሾ አወረድንላችሁ አላለቀሳችሁም’ ይሉአቸዋል።


ይህንም ሲነግራቸው ሳለ እነሆ አንድ ገዢ መጥቶ እየሰገደ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” አለው።


ከምኲራብ አለቆች አንዱ ኢያኢሮስ የተባለው፥ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቆ፥


ወደ ውስጥ ገብቶም፥ “ይህን ያህል ለምን ትታወካላችሁ ለምን ታለቅሳላችሁ? ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።


ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት፤ መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ።