ማርቆስ 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኞቹ ሸሽተው ሄዱ፤ በከተማና በገጠርም አወሩ፤ ሕዝቡም የሆነውን ለማየት መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞቹ ሸሽተው ሄዱ፤ ወሬውን በከተማና በገጠር አዳረሱት፤ ሕዝቡም የሆነውን ለማየት ካለበት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐሣማዎቹ እረኞች ሸሽተው ሄዱ፤ በከተማና በገጠር ወሬውን አወሩ፤ ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ከየቤታቸው ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ። |
እርሱም ፈቀደላቸው። ርኩሳን መናፍስቱም ወጥተው በዐሣማዎቹ ገቡ፤ ሁለት ሺህ ያህል ዐሣማዎችም በርግገው ከገደሉ አፋፍ ወደ ባሕሩ ተወረወሩ፤ በባሕሩ ውስጥም ሰጠሙ።
ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ፥ የአጋንንት ሠራዊት አድረውበት የነበረው ሰው፥ ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ ፍርሃትም አደረባቸው።