ማርቆስ 3:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም መልሶ፣ “እናቴ ማን ናት፣ ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልሶም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሶም፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው? አላቸው። |
ይህ ዐናጢው አይደለምን? የማርያም ልጅ፥ የያዕቆብና የዮሳ፥ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።