ማርቆስ 11:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ከሰማይ ነው” ብንል፥ “ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?” ይለናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ ‘ከሰማይ ነው’ ብንል፣ ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “እንግዲህ ምን እንበል?” በማለት እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ “ ‘ከእግዚአብሔር ነው፥’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ “‘ከሰማይ ነው፤’ ብንል ‘እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ነው ብንል፦ እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤ |
ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፤ እንዲህም ብሎ ጮኸ “‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤’ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።”