ማርቆስ 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምካት በለስ ደርቃለች” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምሃት በለስ ደርቃለች!” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስም ነገሩ ትዝ ብሎት ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት ዛፍ ደርቃለች” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም ትዝ ብሎት “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም ትዝ ብሎት፦ መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው። |
በመንገድ ዳር የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን ከቅጠል በስተቀር ምንም አላገኘባትም፤ “እንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስዋ ዛፍም ወዲያውኑ ደረቀች።
ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።