ማርቆስ 1:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ለምጻምም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፥ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ለምጻም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ለምጻም ወደ ኢየሱስ መጣና በእግሩ ሥር ተንበርክኮ፦ “ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና “ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ብሎ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና፦ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። |
ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ከኢዮአብ ቤት ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት፥ በምርኲዝ የሚሄድ አንካሳ፥ ወይም በሰይፍ ተመቶ የሚሞት ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ አይታጣ።”
በኋላም እግዚአብሔር በዖዝያ ላይ የቆዳ በሽታ አሳደረበት፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ይህ በሽታ ስላልለቀቀው ከሥራው ሁሉ ተገልሎ በተለየ ቤት ውስጥ ለብቻው ይኖር ነበር፤ በዚህም ጊዜ መንግሥቱን ሲመራ የቆየው ልጁ ኢዮአታም ነበር።
ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቆያለን?
ሰሎሞንም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መደገፊያ ሠርቶ በአደባባዩ መካከል ተክሎት ነበር፥ በእርሱም ላይ ቆመ፥ በእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጉልበቱ ተንበርክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ፥
ከዚያ ተነሥቶ መንገዱን ሲጀመር፥ አንድ ሰው ወደ እርሱ እየሮጠ መጣ፤ በፊቱም በጉልበቱ ተንበርክኮ፥ “ቸር መምህር ሆይ፤ የዘለዓለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይገባኛል” አለው።
ተንበርክኮም “ጌታ ሆይ! ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።