La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 9:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ “መምህር ሆይ! ለእኔ ብቸኛ ልጄ ነውና፥ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “መምህር ሆይ፤ ያለኝ ልጅ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጮኸ! “መምህር ሆይ፥ ይህ ለኔ አንድ ልጅ ነውና እንድታድንልኝ እለምንሃለሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንድ ሰውም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጮኾ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ እርሱ ለእኔ አንድ ነውና ልጄን ታይ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ አንድ ልጅ ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 9:38
8 Referencias Cruzadas  

እኛም፥ ‘አዎን፥ ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፤ ወንድምየው ሞቷል፤ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር።


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


እነሆ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አገር መጥታ “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ ማረኝ፤ ሴት ልጄ በጋኔን ክፉኛ ተይዛለች” እያለች ጮኸች።


ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ አንድ የሞተ ሰው ተሸክመው እያወጡ ነበር፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ እርሷም መበለት ነበረች፤ የከተማይቱም ብዙ ሕዝብ ከእርሷ ጋር አብረው ነበሩ።


በማግስቱም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኘው።


እነሆም፥ ርኩስ መንፈስ ይይዘዋል፤ ድንገትም ይጮኻል፤ አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ አድቅቆ በጭንቅ ይለቀዋል፤


እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደመጣ ሰምቶ፥ ልጁ ሊሞት ስለ ቀረበ፥ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው።