ሉቃስ 8:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይህን እየተናገረ ሳለ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ገና ይህንን በመናገር ላይ ሳለ አንድ ሰው ከምኲራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን በከንቱ አታድክመው!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅህስ ሞታለች እንግዲህ መምህሩን አታድክመው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ገና ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም አለ። |
ይህንም ሲነግራቸው ሳለ እነሆ አንድ ገዢ መጥቶ እየሰገደ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” አለው።
ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ። ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ መቶ አለቃው ወዳጆቹን ወደ እርሱ ልኮ እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና ራስህን አታድክም፤