ሉቃስ 22:58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አይቶት “አንተም እኮ ከእነርሱ አንዱ ነህ፤” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው! አይደለሁም፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላም አንድ ሌላ ሰው አይቶት፣ “አንተም ደግሞ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አለው። ጴጥሮስ ግን፣ “አንተ ሰው፤ እኔ አይደለሁም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው ጴጥሮስን አየውና “አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ!” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው! አይደለሁም!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አየውና፥ “አንተም ከእነርሱ ወገን ነህ” አለው፤ ጴጥሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! እኔ አይደለሁም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሌላው አይቶት፦ አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አለው። ጴጥሮስ ግን፦ አንተ ሰው፥ እኔ አይደለሁም አለ። |
ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች መካከል አንዱ፥ ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ፥ “በአትክልቱ ስፍራ ከእርሱ ጋር አይቼህ አልነበረምን?” አለው።