ሉቃስ 20:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቡም ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ በመልሱም እየተደነቁ ዝም አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በተናገረው ቃል በሕዝቡ ፊት ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ በመልሱም ተገርመው ዝም አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ ስለዚህ በመልሱ ተደንቀው ዝም አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቡም ሁሉ ፊት በአነጋገሩ ማሳሳት ተሳናቸው፤ መልሱንም አድንቀው ዝም አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቡም ፊት በቃሉ ሊያጠምዱት አልቻሉም በመልሱም እየተደነቁ ዝም አሉ። |
ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ይከተሉት የነበሩትን እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።
ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤