La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 20:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ መልኩና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። ሲመልሱም “የቄሣር ነው” አሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እስኪ አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ በላዩ ያለው የማን መልክና ጽሕፈት ነው?” እነርሱም፣ “የቄሳር ነው” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እስቲ ገንዘቡን አሳዩኝ፤ በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” እነርሱም “የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው” አሉት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ጥ​ተ​ውም አሳ​ዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕ​ፈ​ቱስ የማ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የቄ​ሣር ነው” ብለው መለ​ሱ​ለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መልኩ ጽሕፈቱስ የማን ነው? አላቸው። መልሰውም፦ የቄሣር ነው አሉት።

Ver Capítulo



ሉቃስ 20:24
14 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ያ ባርያ ከዚያ ወጥቶ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን ከባልንጀሮቹ ባርያዎች አንዱን አገኘና ‘ዕዳህን ክፈለኝ’ ብሎ አንቆ ያዘው።


ከሠራተኞቹ ጋር በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ቦታ ሰደዳቸው።


እርሱም “ይህ መልክና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው።


እነርሱም አመጡለት፥ “ይህ የማን መልክ ነው? ጽሕፈቱስ የማን ነው?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “የቄሣር ነው” አሉት።


በዚያም ወራት የመላው ዓለም ሕዝብ እንዲመዘገቡ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣ።


ለቄሣር ግብር እንድንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት።


እርሱ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦


እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው።


“ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር።


ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፥ ጴንጤናዊው ጲላጦስም የይሁዳ ገዥ ነበር፥ ሄሮድስ የገሊላ አገረ ገዥ፥ ወንድሙ ፊልጶስ ደግሞ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አገረ ገዢ፥ ሊሳኒዮስም የአቢሊኒ አገረ ገዢ ሳሉ፥


ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።


አግሪጳም ፈስጦስን “ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር፤” አለው።


ቅዱሳን ሁሉ ይልቁንም ከቄሣር ቤት የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።