ሉቃስ 20:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይመጣል እነዚህንም ተከራዮች ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።” ይህንንም በሰሙ ጊዜ “ይህስ በጭራሽ አይሁን፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥቶ እነዚያን ገበሬዎች ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለሌሎች ይሰጣል።” ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ “እንዲህ ያለውንስ አያምጣው” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይኑ ተክል ባለቤት ራሱ ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ይገድላል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጣል።” ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይኑ ባለቤት በመጣ ጊዜ እንግዲህ ምን ያደርጋቸዋል? ይመጣል፤ እነዚያንም ገባሮች ይገድላቸዋል፤ ወይኑንም ለሌሎች ገባሮች ይሰጣል፤” ቃሉንም ሰምተው፥ “አይሆንም፤ እንዲህ አይደረግም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይመጣል እነዚህንም ገበሬዎች ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል። ይህንም በሰሙ ጊዜ፦ ይህስ አይሁን አሉ። |
ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።
ተመልሰው መዳን እስከማይችሉ ድረስ ተሰናከሉን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በጭራሽ! ነገር ግን እነርሱን ለማስቀናት፥ በእነርሱ በደል፥ መዳን ለአሕዛብ ሆነ።
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።
እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።
እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? በጭራሽ! ነገር ግን በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር፤ ሕጉ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞትን አላውቅም ነበር።
ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል እንደሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን የአካል ክፍሎች ወስጄ የአመንዝራ ክፍሎች አካል ላድርጋቸውን? ፈጽሞ ከቶ አይገባም።
ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ፥ እኛ ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ብንገኝ፥ ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነውን? በጭራሽ አይደለም።
እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤