ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ።
ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የተወደደ ሆኖ፥ በጥበብና በቁመት እያደገ ይሄድ ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም በእግዚአብሔር ዘንድ፥ በሰውም ዘንድ፥ በጥበብና በአካል በሞገስም አደገ።
ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።
ሕፃኑም አደገ ጠነከረም፤ ጥበብም ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።
እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገልግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
ብላቴናው ሳሙኤልም እያደገና፥ በጌታም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ።