ዘሌዋውያን 19:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሥዋዕታችሁን በሠዋችሁበት ዕለትና በማግስቱ ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ማናቸውም ነገር ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሥዋዕቱም ባቀረባችሁት ዕለት ወይም በማግስቱ ይበላ፤ እስከ ሦስተኛው ቀን የተረፈ ማንኛውም ነገር ይቃጠል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውም እንስሳው በታረደበት ዕለት ወይም በማግስቱ መበላት አለበት፤ እስከ ሦስተኛው ቀን ተርፎ የቈየ ማናቸውም ሥጋ በእሳት ይቃጠል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምትሠዉበት ቀንና በነጋው ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምትሠውት ቀንና በነጋው ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። |