ዘሌዋውያን 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለጌታ ምስጋና የተለየ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛውም ዓመት ፍሬው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የምስጋና መሥዋዕት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ዓመት እኔን እግዚአብሔርን ታመሰግኑበት ዘንድ ለእኔ የተለየ ስጦታ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ቅዱስ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ቅዱስ ይሁን። |
“ወደ ምድሪቱም ገብታችሁ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁ ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት ለእናንተ እንዳልተገረዘ ይሆናል፤ አይበላም።