ዘሌዋውያን 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማናቸውም ሰው በባርነት ሥር ካለች ሴት ጋር ቢተኛ፥ እርሷም ለሌላ ሰው ታጭታ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ያልተዋጀች ወይም አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ይህ አድራጎት ቅጣት ይረኖረዋል፤ ሆኖም አርነት አልወጣችምና አይገደሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው ለሌላ ከታጨች ሴት ባሪያ ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ሴቲቱም ያልተዋጀች ወይም ነጻ ያልወጣች ብትሆን ይቀጣል፤ ነገር ግን ሴቲቱ ነጻ ስላልወጣች አይገደሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ልጃገረድ የሆነች አገልጋዩን ለሌላ ሰው ቊባት ትሆን ዘንድ ለመሸጥ ካስማማ በኋላ ገዢው ገንዘቡን ከፍሎ ከመጨረሱ በፊት ሻጩ ከልጃገረዲቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ ሁለቱም ይቀጣሉ፤ ሆኖም እርስዋ ገና ነጻ ያልወጣች አገልጋዩ ስለ ሆነች የሞት ቅጣት አይፈጸምባቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እርስዋም ለባል የተሰጠች፥ ዋጋዋም ያልተከፈለ፥ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ቅጣት አለባቸው፤ አርነት አልወጣችምና አይገደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እርስዋም ለባል የተሰጠች ዋጋዋም ያልተከፈለ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ቅጣት አለባቸው፤ አርነት አልወጣችምና አይገደሉም። |