La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 15:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈሳሽ ነገር ያለበትን ሰው ገላውን የሚነካ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን ሰው የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፈሳሽ ያለበትን ሰው የሚነካ ሁሉ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ፥ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈሳሽ ነገር ያለ​በ​ትን የሰ​ውን ሥጋ የሚ​ነካ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈሳሽ ነገር ያለበትን የሰውን ሥጋ የሚነካ ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 15:7
7 Referencias Cruzadas  

“በእነዚህም የረከሳችሁ ትሆናላችሁ፤ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


በድናቸውንም የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


“ለምግብነት ከምታውሉት እንስሳ የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው በተቀመጠበት በማናቸውም ነገር ላይ የሚቀመጥበት ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው በንጹሕ ሰው ላይ ቢተፋ፥ የተተፋበት ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም የሚርመሰመስ ፍጥረት፥ ወይም ርኩሰቱ ማናቸውም ዓይነት ሆኖ የሚያረክሰውን ሰው የሚነካ፥


የረከሰውም ሰው የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።”