ፈሳሹም ነገር በሚፈስስበት ጊዜያት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በወር አበባዋ ጊዜ እንደነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ እንደ ወር አበባዋ ርኩስነት ርኩስ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንዲትም ሴት ከወር አበባዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከወር አበባዋ ጊዜያት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ ፈሳሹ ነገር በሚፈስስበት ቀን ሁሉ በርኩስነትዋ ትቀጥላለች፤ በወር አበባዋ ጊዜያት እንደ ሆነች እንዲሁ እርሷ ርኩስ ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ሴት ከወር አበባዋ ጊዜ ሌላ ብዙ ቀን ደም ቢፈስሳት፣ ወይም የወር አበባዋ ጊዜ ካለፈ በኋላ የደሙ መፍሰስ ባይቋረጥ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ፣ ደም መፍሰሱ እስኪቆም ድረስ ርኩስ ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንዲት ሴት ከወር አበባዋ ወቅት አልፎ ለብዙ ቀን የሚፈስ ወይም ከተመደበው የወር አበባዋ በኋላ ባለማቋረጥ የሚፈስ ደም ቢኖራት፥ ደሙ እስከሚቆምበት ጊዜ ድረስ ልክ በወር አበባዋ ጊዜ እንደ ነበረችበት ሁኔታ የረከሰች ትሆናለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሴትም ከግዳጅዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከግዳጅዋ ወራት በኋላ ቢፈስስ፥ በግዳጅዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ ርኩስነት ወራት ትሆናለች፤ ርኵስት ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴትም ከመርገም ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከመርገምዋ ወራት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ በመርገምዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ ርኵስነት ወራት ትሆናለች፤ ርኩስ ናት። |
ፈሳሹም ነገር በሚፈስስበት ጊዜያት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በወር አበባዋ ጊዜ እንደነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ እንደ ወር አበባዋ ርኩስነት ርኩስ ይሆናል።
ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።