ዘሌዋውያን 15:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሩ የነካው ልብስ ሁሉ ቆዳም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈሰሰው ዘር የነካው ማንኛውም ልብስ ወይም ቍርበት በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሩ የፈሰሰበት ማንኛውም ልብስም ሆነ ቆዳ በውሃ ይታጠብ እርሱም እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘር የነካው ልብስ ሁሉ፥ ቍርበትም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘር የነካው ልብስ ሁሉ ቍርበትም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። |
ከአሮን ዘር ማናቸውም ሰው የለምጽ ደዌ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት፥ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሱት ነገሮች አይብላ። በበድን፥ ወይም ዘሩ በሚፈስስበት ሰው የረከሰውን ነገር የሚነካ፥
በእሳት ለማለፍ የሚችለውን ሁሉ በእሳት ታሳልፉታላችሁ፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በማንጻት ውኃ ደግሞ ይጠራል። በእሳትም ለማለፍ የማይችለውን በውኃ ታሳልፉታላችሁ።