ዘሌዋውያን 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው እጁን በውኃ ሳይታጠብ ማንንም ሰው ቢነካ፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው እጁን በውሃ ሳይታጠብ ሌላውን ሰው ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሳሽ ያለበት ሰው እጁን ሳይታጠብ አንድን ሰው ቢነካ ያ ሰው ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው እጁን በውኃ ሳይታጠብ የሚነካው ሁሉ ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው እጁን በውኃ ሳይታጠብ የሚነካው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። |
እርሱም ከተቀመጠበት በታች ያለውን ማናቸውንም ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።