መሳፍንት 9:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሜሌክም በዚያ መመሸጋቸውን ሲሰማ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም በሴኬም ግንብ ገዦች ሁሉ መመሸጋቸውን ሲሰማ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክም በሴኬም መሰብሰባቸውን ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአቤሜሌክም በሰቂማ ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰበሰቡ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሜሌክም በሴኬም ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰበሰቡ ሰማ። |
እርሱና ሰዎቹ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፤ አቤሜሌክም መጥረቢያ ወስዶ ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ በትከሻውምላይ አደረገ። የተከተሉትንም ሰዎች፥ “ፍጠኑ፤ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን አድርጉ” ሲል አዘዛቸው።