ከዚያም ዜቡል፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜልክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልካቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።
መሳፍንት 9:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገዓል የሴኬምን ሰዎች መርቶ በመውጣት አቤሜሌክን ተዋጋው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዓል የሴኬምን ገዦች መርቶ በመውጣት አቢሜሌክን ተዋጋው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጋዓል የሴኬምን ሰዎች እየመራ ወጥቶ አቤሜሌክን ጦርነት ገጠመው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገዓልም በሰቂማ ሰዎች ፊት ወጣ፤ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገዓልም በሴኬም ሰዎች ፊት ወጣ፥ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ። |
ከዚያም ዜቡል፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜልክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልካቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።