መሳፍንት 9:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአቤድ ልጅ ገዓል ከከተማይቱ ወጥቶ በመግቢያው በር ላይ ሲቆም፥ አቤሜሌክና ሰዎቹ ካደፈጡበት ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአቤድ ልጅ ገዓል ከከተማዪቱ ወጥቶ በመግቢያው በር ላይ ሲቆም፣ አቢሜሌክና ሰዎቹ ካደፈጡበት ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክና ተከታዮቹ የዔቤድ ልጅ ጋዓል ወጥቶ በከተማይቱ ቅጽር በር መቆሙን ባዩ ጊዜ ከሸመቁባቸው ስፍራዎች ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋም ጊዜ የአቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማዪቱ መግቢያ በር ቆመ፤ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብም ከሸመቁበት ስፍራ ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአቤድም ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማይቱ በር አደባባይ ቆመ፥ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ ከሸመቁበት ስፍራ ተነሱ። |
ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፥ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፥ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ ነው” አለው።