መሳፍንት 9:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አቤሜልክም መልእክተኞች በምስጢር ልኮ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተው ከተማይቱ እንድትሸፍትብህ አድርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ አቢሜሌክም መልእክተኞች በምስጢር ልኮ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተው ከተማዪቱ እንድትሸፍትብህ አድርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአሩማ ወዳለውም ወደ አቤሜሌክ መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት አሳሰባቸው፥ “የዔቤድ ልጅ ጋዓል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም መጥቶአል፤ በአንተም ላይ የከተማውን ሕዝብ አነሣሥቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ብሎ ወደ አቤሜሌክ ከእጅ መንሻ ጋር መልእክተኞችን ላከ፥ “እነሆ፥ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሰቂማ መጥተዋል፤ እነሆም፥ በአንተ ምክንያት ከተማዪቱን ይወጓታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ብሎ ወደ አቤሜሌክ በተንኮል መልክተኞች ላከ፦ እነሆ፥ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተዋል፥ በአንተም ላይ ከተማይቱን አሸፍተዋል። |