ከዚህም ሌላ አቤሴሎም፥ “በምድሪቱ ላይ ዳኛ እኔ በሆንኩ ኖሮ! አቤቱታ ወይም ክስ ያለበት ሁሉ ወደ እኔ ሲመጣ፥ ፍትሕ እንዲያገኝ ባደረግሁ ነበር” ይል ነበር።
መሳፍንት 9:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምነው ይህን ሕዝብ የማዘው እኔ በሆንሁ ኖሮ፥ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፤ ‘ሠራዊትህን አብዝተህ እስቲ ውጣ! እለው ነበር።’” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምነው ይህን ሕዝብ የማዝዘው እኔ በሆንሁ ኖሮ! አቢሜሌክን አስወግደው ነበር፤ ‘ሰራዊትህን አብዝተህ ውጣ!’ እለው ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሕዝብ የምመራው እኔ በሆንኩ ኖሮ! አቤሜሌክን ወዲያ አስወግደው ነበር፤ ደግሞም ‘ሠራዊትህን በማጠንከር ወጥተህ ተዋጋ!’ ብዬ እነግረው ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤሜሌክን አሳድደው ነበር” አለ። አቤሜሌክንም፥ “ሠራዊትህን አብዝተህ ና፤ ውጣ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምንስ ለዚህ እንገዛለን? ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤሜሌክን አሳድደው ነበር አለ። አቤሜሌክንም፦ ሠራዊትህን አብዝተህ ና፥ ውጣ አለው። |
ከዚህም ሌላ አቤሴሎም፥ “በምድሪቱ ላይ ዳኛ እኔ በሆንኩ ኖሮ! አቤቱታ ወይም ክስ ያለበት ሁሉ ወደ እኔ ሲመጣ፥ ፍትሕ እንዲያገኝ ባደረግሁ ነበር” ይል ነበር።
ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።
ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ ና ይዋጣልን!” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤