መሳፍንት 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የአቤድ ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም መጣ፤ የሴኬምም ሰዎች ተማመኑበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የአቤድ ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋራ ወደ ሴኬም መጣ፤ የሴኬምም ገዦች ተማመኑበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የዔቤድ ልጅ ጋዓል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም መጣ፤ የሴኬምም ሰዎች እምነታቸውን በእርሱ ላይ ጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአቤድም ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋር መጣ፤ የሰቂማ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአቤድም ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋር መጥቶ ወደ ሴኬም ገባ፥ የሴኬምም ሰዎች ታመኑበት። |
የሴኬም ነዋሪዎችም አቤሜሌክን ሸምቀው የሚጠባበቁትን ሰዎች መደቡ፤ ሰዎቹም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በዚያ የሚያልፈውን ሁሉ ዘረፉ፤ ወሬውም ለአቤሜሌክ ደረሰው።
የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቤሜሌክ እንገዛለን?