ከዚያም ዛፎቹ የወይን ተክልን፥ “መጥተህ ንጉሣችን ሁን” አሉት።
“ከዚያም ዛፎቹ የወይን ተክልን፣ ‘መጥተህ ንጉሣችን ሁን’ አሉት።
ስለዚህ ዛፎቹ የወይን ተክልን ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት።
ዛፎችም ሁሉ ወይኑን፦ መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት።
ዛፎችም ውይኑን፦ መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት።
በለስ ግን፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እጅግ ጣፋጭና መልካም የሆነውን ፍሬዬን መስጠት ልተውን?” አለ።
የወይን ተክሉም፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ አማልክትንና ሰዎችን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጄን መስጠት ልተውን?” አለ።