መሳፍንት 6:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደገና ልጠይቅ። በጠጉሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደ ገና ልጠይቅ። በጠጕሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ እንደገና አንድ ጊዜ እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ይኸውም በበግ ጠጒሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ምልክት እንዲታይ ልጠይቅ፤ በዚህን ጊዜ የጠጒሩ ባዘቶ ደረቅ ሆኖ በዙሪያው ያለው ምድር እርጥብ እንዲሆን አድርግልኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም እግዚአብሔርን አለው፥ “በቍጣህ አትቈጣኝ፤ ደግሞ አንዲት ነገር ልናገር፤ ጠጕሩ ብቻውን ደረቅ ይሁን፤ በምድሩም ላይ ጠል ይውረድ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እኔ ይህን አንድ ጊዜ ስናገር አትቈጣኝ፥ እኔ ይህን አንድ ጊዜ በጠጉሩ፥ እባክህ፥ ልፈትን፥ አሁንም በጠጉሩ ብቻ ላይ ደረቅ ይሁን፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ጠል ይሁን አለው። |
እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።
ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።