መሳፍንት 6:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ “እንደ ተናገርከው እስራኤልን በእኔ እጅ ታድን ዘንድ መርጠኸኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፥ “እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ እነሆ፥ በአውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ጠጉር አኖራለሁ፥ በጠጉሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንድታድናቸው አውቃለሁ አለ። |
ኢሳይያስም “እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የሚፈጽም ስለ መሆኑ ራሱ ምልክት ይሰጥሃል፤ እንግዲህ አሁን የምትመርጠው ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ነው? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ?” ሲል ጠየቀው።
በዚህ ጊዜ ጌታ ወደ እርሱ ዘወር ብሎ፥ “ባለህ ኃይል ሂድ፤ እስራኤውያንን ከምድያማውያን እጅ ነጻ እንድታወጣ የምልክህ እኔ አይደለሁምን? አለው”
እነሆ፤ የበግ ጠጉር ባዘቶ በአውድማው ላይ አኖራለሁ። ምድሩ በሙሉ ደረቅ ሆኖ ባዝቶው ላይ ብቻ ጤዛ ቢኖር፥ እንዳልከው እስራኤላውያንን በእኔ እጅ እንደምታድናቸው አውቃለሁ።”