መሳፍንት 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባራቅም፥ “አብረሽኝ የምትሄጂ ከሆነ እሄዳለሁ፤ አብረሽኝ የማትሄጂ ከሆነ ግን አልሄድም” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባርቅም፣ “ዐብረሽኝ የምትሄጂ ከሆነ እሄዳለሁ፤ ዐብረሽኝ የማትሄጂ ከሆነ ግን አልሄድም” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ባራቅ “አንቺ ከእኔ ጋር ከሄድሽ እሄዳለሁ፤ አብረሽኝ ካልሄድሽ ግን እኔም አልሄድም” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባርቅም፥ “አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም፤ እግዚአብሔር መልአኩን ከእኔ ጋር የሚልክበትን ዕለት አላውቃትምና” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርቅም፦ አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፥ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም አላት። |
ዲቦራ መልሳ፥ “ይሁን እሺ፤ መሄዱን አብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ ጌታ ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፤