መሳፍንት 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር፥ በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ነበር፤ እስራኤላውያንም ለፍርድ ወደ እርሷ ይመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር፣ በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ነበር፤ እስራኤላውያንም ለፍርድ ወደ እርሷ ይመጡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችም ነቢይት በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤትኤል መካከል በሚገኘው የዲቦራ የተምር ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ስለ ነበር የእስራኤል ሕዝብ ፍርድ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይሄዱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በኤፍሬም ተራራ በቤቴልና በኢያማ መካከል “የዲቦራ ዘንባባ” ተብሎ በሚጠራው ዛፍ ሥር ተቀምጣ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እርስዋ ለፍርድ ይወጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዛፍ ከሚባለው ከዘንባባው በታች ተቀምጣ ነበር፥ የእስራኤልም ልጆች ወደ እርስዋ ለፍርድ ይወጡ ነበር። |
አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቡን አቅርብ፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አቅርብ፤
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።”
በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ።
ሳኦልም፥ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፥ በጊብዓ ኰረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር፥ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።
ሳሙኤልም ሞተ፤ መላው እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ ራማ ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።