ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ “መንገድ ተሳስታችኋል፤ የምትፈልጓት ከተማ ይህች አይደለችም፤ ይልቅስ ወደምትፈልጉት ሰው እኔ ልመራችሁ ስለምችል ተከተሉኝ” ብሎ ወደ ሰማርያ መራቸው።
መሳፍንት 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበ ለችውና፥ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበለችውና፣ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዔልም ሲሣራን ልትቀበለው ወጥታ “ጌታዬ ና፥ ወደ ድንኳኔ ግባ፤ ከቶ አትፍራ” አለችው፤ እርሱም ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ በልብስ ሸፈነችው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያዔልም ሲሣራን ለመቀበል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አትፍራም” አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ በምንጣፍም ሸፈነችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጥታ፦ ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፥ አትፍራ አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፥ በመጎናጸፊያዋም ሸፈነችው። |
ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ “መንገድ ተሳስታችኋል፤ የምትፈልጓት ከተማ ይህች አይደለችም፤ ይልቅስ ወደምትፈልጉት ሰው እኔ ልመራችሁ ስለምችል ተከተሉኝ” ብሎ ወደ ሰማርያ መራቸው።
በሐጾር ንጉሥ በየቡስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደ ሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ሮጠ።