መሳፍንት 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የእልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቊልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፥ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የዕልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቍልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፣ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቈየት የሚገባቸውን ያኽል በውጪ ቈዩ፤ ነገር ግን አሁንም በሩ እንዳልተከፈተ ባዩ ጊዜ ቊልፉን ወስደው በሩን ከፈቱ፤ እዚያም ጌታቸው ሞቶ በወለል ላይ መዘርጋቱን ተመለከቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪያፍሩም ድረስ ቈዩ፤ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ፤ እነሆም፥ ጌታቸው በምድር ላይ ወድቆ ሞቶም አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪያፍሩም ድረስ እጅግ ዘገዩ፥ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ፥ እነሆም፥ ጌታቸው በምድር ወድቆ ሞቶም አገኙት። |