ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ።
መሳፍንት 3:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሁድ ከሄደ በኋላ፥ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፥ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፥ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናዖድ ከሄደ በኋላ፣ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፣ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፣ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሁድ ከሄደ በኋላ የንጉሡ አገልጋዮች መጥተው በሮቹ እንደ ተቈለፉ አዩ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከውስጥ በኩል በመጸዳዳት የዘገየ መሰላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናዖድም ከሄደ በኋላ አገልጋዮቹ መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምናልባት በበጋ ሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዖድም ከሄደ በኋላ ባሪያዎቹ መጡ፥ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፦ ማናልባት በሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል አሉ። |
ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ።
እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የእልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቊልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፥ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት።
ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዓለት” ወደ ተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።