መሳፍንት 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጉባኤውም መሪዎች እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ የብንያም ሴቶች አልቀዋል፤ ታዲያ ለቀሩት ወንዶች ሚስት የምናገኝላቸው እንዴት ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጉባኤውም ሽማግሌዎች እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ የብንያም ሴቶች ዐልቀዋል፤ ታዲያ ለቀሩት ወንዶች ሚስት የምናገኝላቸው እንዴት ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የጉባኤው መሪዎች እንዲህ አሉ፥ “በብንያም ነገድ ከእንግዲህ ሴቶች አልተገኙም፤ ታዲያ ከሞት የተረፉት ወንዶች ሚስት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ምን እናድርግ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማኅበሩ ሽማግሌዎችም፥ “ከብንያም ሴቶች ጠፍተዋልና የቀሩት ስዎች ሚስት እንዲያገኙ ምን እናደርጋለን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማኅበሩ ሽማግሌዎች፦ ከብንያም ሴቶች ጠፍተዋልና የቀሩት ሰዎች ሚስት እንዲያገኙ ምን እናደርጋለን? አሉ። |