መሳፍንት 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልእክተኞቹም እንዲህ አሏቸው፤ “ምድሪቱ እጅግ መልካም መሆኗን አይተናል፤ እንግዲህ ተነሡ ሄደን እንዋጋቸው፤ ተነሡ እንጂ ዝም ትላላችሁን? ወደዚያው ሄዳችሁ ምድሪቱን ለመያዝ አታመንቱ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኞቹም እንዲህ አሏቸው፤ “ምድሪቱ እጅግ መልካም መሆኗን አይተናል፤ እንግዲህ ተነሡ! ሄደን እንዋጋቸው፤ ተነሡ እንጂ ዝም ትላላችሁን? ወደዚያው ሄዳችሁ ምድሪቱን ለመያዝ አታመንቱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “እንግዲህ ኑ! በላዪሽ ላይ አደጋ እንጣል! ምድሪቱ በጣም ጥሩ መሆንዋን አይተናል፤ እዚህ ያለ ሥራ ቦዝናችሁ አትቀመጡ፤ ይልቅስ በፍጥነት ሄዳችሁ ያዙአት! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናል፤ ተነሡ፤ በእነርሱ ላይ እንውጣ፤ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናልና ተነሡ፥ በእነርሱ ላይ እንውጣ፥ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ። |
ሚክያስም “እንግዲህ የተወሰነው ይህ ነው፤ እነዚህን የአንተን ነቢያት የሐሰት ቃል እንዲነግሩህ ያደረጋቸው ጌታ ነው፤ ስለዚህ በአንተ ላይ መዓት ሊያመጣብህ ጌታ ራሱ ወስኖአል!” ሲል ንግግሩን ደመደመ።
አክዓብ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለ ሥልጣኖች “በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት!” አላቸው።
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ በርቱ! ወንድነታችሁም ይታይ፤ ያለዚያ ባርያ እንዳደረጋችኋቸው ሁሉ፥ ዕብራውያን እናንተን መልሰው ባርያ ያደርጓችኋል። ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!”