መሳፍንት 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማይቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቸ ጋር መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፥ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማዪቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቹ ጋራ መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፣ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሶምሶን ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ የቈየው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ከዚያን በኋላ ከመኝታው ተነሣ፤ የከተማይቱን ቅጽር በር፥ ሁለቱን ምሶሶዎችና መቈለፊያዎቹን ሁሉ ፈነቃቀለ፤ ያንን ሁሉ በትከሻው ተሸክሞ ከኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኮረብታ ድረስ ወሰደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ በእኩለ ሌሊትም ተነሥቶ የከተማዪቱን በር መዝጊያ ያዘ፤ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያው ጋር ነቀለው፤ በትከሻውም ላይ አደረገ፤ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፤ በዚያም ጣለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፥ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሥቶ የከተማይቱን በር መዝጊያ ያዘ፥ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያውም ጋር ነቀለው፥ በትከሻውም ላይ አደረገ፥ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ በዚያም ጣለው። |
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጡ፤ ንጉሣቸው በፊታቸው ሄዷል፥ ጌታም በራሳቸው ላይ ነው።
የጋዛ ሰዎች፥ “ሳምሶን እዚህ ነው!” የሚል ወሬ ደረሳቸው፤ ስለዚህም ሰዎቹ ቦታውን ከበው፤ ሌሊቱን በሙሉ በከተማይቱ ቅጥር በር ላይ አድፍጠው ጠበቊት፤ “በማለዳ እንገድለዋለን” በማለትም ሌሊቱን በሙሉ እንዳደፈጡ አደሩ።