እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
መሳፍንት 16:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሊላ፥ ሳምሶንን በጭኗ ላይ አስተኝታ እንቅልፍ እንዲወስደው ካደረገች በኋላ አንድ ሰው ጠርታ ሰባቱን የጠጉር ቈንዳላዎቹን አስላጨቻቸው፤ እርሷም ታስጨንቀው ጀመር፤ ኃይሉም ተለየው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሊላ፣ ሳምሶንን በጭኗ ላይ አስተኝታ እንቅልፍ እንዲወስደው ካደረገች በኋላ አንድ ሰው ጠርታ ሰባቱን የጠጕር ሹሩባዎቹን አስላጨቻቸው፤ እርሷም ታስጨንቀው ጀመር፤ ኀይሉም ተለየው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደሊላ ሶምሶንን በጭንዋ ላይ አስተኝታ፤ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገች። አንድ ሰውም ጠርታ ሰባቱን የጠጒሩን ቁንዳላዎች እንዲቈረጡ አደረገች፤ ኀይሉም ከእርሱ ተለይቶት ስለ ነበር በማዋረድ ታስጨንቀው ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በጕልበቷ ላይ አስተኛችው፤ ጠጕር ቈራጭም ጠራች፤ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን ላጨው። ይደክምም ጀመረ፤ ኀይሉም ከእርሱ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በጉልበትዋ ላይ አስተኛችው፥ አንድ ሰውም ጠራች፥ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጉንጉን ላጨው። ልታዋርደውም ጀመረች፥ ኃይሉም ከእርሱ ሄደ። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ደሊላ ሁሉንም ነገር እንደ ነገራት በተረዳች ጊዜ፥ ለፍልስጥኤማውያን ገዦች “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና ተመልሳችሁ ኑ” ብላ ላከችባቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም ብሩን ይዘው ተመልሰው መጡ።
እርሷም፥ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፥ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን ጌታ እንደ ተወው አላወቀም ነበር።