መሳፍንት 14:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥቂት ቀን በኋላም ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም በድን ለማየት ከመንገድ ዘወር አለ፤ በበድኑም ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮ ተመለከተ፤ ማርም ነበረበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ቀን በኋላም ሊያገባት ተመለሰ። የአንበሳውንም በድን ለማየት ከመንገድ ዘወር አለ፤ በበድኑም ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮ ተመለከተ፤ ማርም ነበረበት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ቀኖች በኋላ እርስዋን ለማግባት ወደዚያ ተመልሶ ሄደ፤ በጒዞም ላይ ሳሉ ያንን የገደለውን አንበሳ ሁኔታ ለማየት ከመንገድ ዞር አለ፤ በድኑን ንቦች ሰፍረውበት በውስጡም ማር. መኖሩን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ተደነቀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም ሬሳ ያይ ዘንድ ከመንገድ ፈቀቅ አለ፤ እነሆም፥ በአንበሳው አፍ ውስጥ ንብ ሰፍሮበት ነበር፤ ማርም ነበረበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥቂትም ቀን በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፥ የአንበሳውንም ሬሳ ያይ ዘንድ ከመንገድ ፈቀቅ አለ፥ እነሆም፥ በአንበሳው ሬሳ ውስጥ ንብ ሰፍሮበት ነበር፥ ማርም ነበረበት። |
እርሱ ይህን ሲያስብ ሳለ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለው “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።