መሳፍንት 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በወጣቶች የተለመደ በነበረው መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በነበረው የሙሽራ ወግ መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቱ ወደ ሴቲቱ ቤት በሄደ ጊዜ፥ ሶምሶን በዚያ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ ይህም ዐይነቱ ግብዣ በወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፤ ጐበዞችም እንዲሁ ያደርጉ ነበርና ሶምሶን በዚያ ሰባት ቀን በዓል አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፥ ጎበዞችም እንዲህ ያደርጉ ነበርና ሶምሶን በዚያ በዓል አደረገ። |
አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ
በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።