የገለዓድ ሕዝብ አለቆችም እርስ በእርሳቸው፥ “በአሞናውያን ላይ ጦርነቱን የሚጀምር ሰው በገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል” ተባባሉ።
መሳፍንት 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮፍታሔ በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት ፈራጅ ሆነ። ገለዓዳዊው ዮፍታሔ ሞተ፤ ከገለዓድም ከተሞች በአንዲቱ ተቀበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮፍታሔ በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት ፈራጅ ሆነ። ገለዓዳዊው ዮፍታሔ ሞተ፤ ከገለዓድም ከተሞች በአንዲቱ ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮፍታሔ ስድስት ዓመት ሙሉ የእስራኤል መሪ ከሆነ በኋላ ሞተ፤ በትውልድ አገሩ በገለዓድ በምትገኘው በአንዲት ከተማ ተቀበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም እስራኤልን ስድስት ዓመት ገዛ። ገለዓዳዊው ዮፍታሔም ሞተ፤ በሀገሩ በገለዓድም ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም በእስራኤል ላይ ስድስት ዓመት ፈረደ። ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ሞተ፥ ከገለዓድም ከተሞች በአንዲቱ ተቀበረ። |
የገለዓድ ሕዝብ አለቆችም እርስ በእርሳቸው፥ “በአሞናውያን ላይ ጦርነቱን የሚጀምር ሰው በገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል” ተባባሉ።
እስቲ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ታዲያ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ ይዘው እዚያው መሻገርያው ላይ ይገድሉታል፤ በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ።