ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ መስራት የሚችሉ ሰዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የዐሥር አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
ኢያሱ 22:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር ዐሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፤እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ጋራ እያንዳንዱን የእስራኤልን ነገድ የሚወክሉ ዐሥር አለቆች ዐብረው ላኩ፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው ከእስራኤላውያን ጐሣዎች የተውጣጡ የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፊንሐስም ጋር ዐሥር ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም እያንዳንዱ በምዕራብ ከሚገኙት ነገዶች የተውጣጡ በየጐሣቸው የቤተሰብ መሪዎች ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር አለቆችም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ አንድ አንድ የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ፤ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፥ እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበረ። |
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ መስራት የሚችሉ ሰዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የዐሥር አለቆች አድርጎ ሾማቸው።