La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 18:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን የጌታ ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ ድርሻ የላቸውም፤ ጋድም ሮቤልም የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የጌታ ባርያ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌዋውያኑ ግን ለእግዚአብሔር የሚሰጡት የክህነት አገልግሎት ርስታቸው ስለ ሆነ በእናንተ መካከል ድርሻ አይኖራቸውም። ጋድ፣ ሮቤልና የምናሴ ነገድ እኩሌታም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምሥራቅ ዮርዳኖስ የሰጣቸውን ርስት ቀደም አድርገው ወስደዋል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይሁን እንጂ የሌዋውያን ድርሻ ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን ማገልገል ስለ ሆነ እነርሱ ከሌሎቻችሁ ጋር የርስት ድርሻ አይኖራቸውም፤ የሮቤልና የጋድ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ርስት አስቀድመው ወርሰዋል።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ እድል ፈንታ የላቸውም፥ ጋድም ሮቤልም የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።

Ver Capítulo



ኢያሱ 18:7
11 Referencias Cruzadas  

ጌታም አሮንን እንዲህ አለው፦ “በምድራቸው ርስት በመካከላቸውም ድርሻ አይኖርህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።


ሌዋውያን ግን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግላሉ፥ እነርሱም የራሳቸውን በደል ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም።


አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”


ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ጌታ ርስቱ ነው።


የጌታ ባርያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የጌታም ባርያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።


ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንደ ነገራቸው እንዲሁ ርስታቸው እርሱ ነው።