La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከየነገዱ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ፤ ተነሥተውም አገሩን ይዞራሉ፥ እንደ ርስታቸውም መጠን ይመዘግቡታል፤ ከዚያም በኋላ ወደ እኔ ይመለሳሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ሰው ምረጡ፤ እኔም ምድሪቱን ተዘዋውረው እንዲያጠኑና እያንዳንዱም ነገድ መውረስ የሚገባውን ድርሻ ዝርዝር መግለጫ ጽፈው እንዲያመጡ እልካቸዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እኔ ይመለሳሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡልኝ፤ እኔም እያንዳንዱ ነገድ ማግኘት የሚገባውን የርስት ድርሻ ለማወቅ የምድሪቱን ሁኔታ አጥንተው እንዲመዘግቡ በመላ አገሪቱ እልካቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው ወደ እኔ ይመጣሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎ​ችን አምጡ፥ ተነ​ሥ​ተ​ውም ሀገ​ሪ​ቱን ይዙ​ሩ​አት፤ ለመ​ክ​ፈ​ልም እን​ዲ​ያ​መች ገል​ጠው ይጻ​ፉ​አት፤ ወደ እኔም ይመ​ለ​ሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከየነገዱ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ፥ ተነሥተውም አገሩን ይዞራሉ፥ እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፥ ወደ እኔም ይመለሳሉ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 18:4
9 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ በጌታ ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።


ከየነገዱም አንድ ሰው የአባቶቹ ቤት አለቃ የሆነ ከእናንተ ጋር ይሁን።


“ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ።”


ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ የሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ እስከ መቼ ቸል ትላላችሁ?


በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል ባለው ግዛት ውስጥ ይቀመጣል፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል ባለው ግዛት ውስጥ ይቀመጣሉ።


እናንተም ምድሩን በሰባት ክፍል ጻፉት፥ የጻፋችሁትንም ወደዚህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በጌታ ፊት በዚህ ዕጣ እጥልላችኋለሁ።


ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ዞሩ፥ በከተሞቹም ልክ በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ በመጽሐፍም ጻፉት፤ ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።


እንግዲህ አሁን ከእስራኤል ነገዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ምረጡ።


“ከሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ምረጥ፤